ራዕይ

የኢየሱስ ክርስቶስን የክብር ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ ለማድረስ የበኩላቸውን ድርሻ በመወጣት ጌታን በተለያዩ የአገልግሎት ክፍሎች በእውቀትና በመረዳት የሚያገለግሉት በቃሉና በመንፈሱ የታጠቁ የወንጌል ሠራተኞችን ተዘጋጅተው ማየት ነው።

ተልዕኮ

መጽሐፍ ቅዱስን የብርሃንና የሥልጣን ምንጭ በማድረግ ክርስቶስን ማዕከል ባደረገ የአቀራረብ ስልት በክርስቶስ ዘላለማዊ ፍቅርና ጸጋ ላይ የሚያተኩሩ አገልጋዮችን ማፍራት ነው።

ዓላማዎች

397063353_349551564412484_2357565127470827610_n

ተማሪዎች መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አውቀት አግኝተው በሚከተሉት አበይት ጉዳዮች ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዲያመጡ ለመርዳት ነው፡-

  • ራሱን ለክርስቶስ ፍጹም ያስገዛና መንፈሳዊ ብስለቱን ያዳበረ እውነተኛ ደቀ መዛሙርትን ለማፍራት፤
  • መጽሐፍ ቅዱስን ብቸኛ የእውነት መሠረት በማድረግ ቃሉን በትክክል የሚተረጉምና በተግባር ላይ የሚያውል ትውልድ ለማስነሳት፤
  • የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚያምንና ክርስቶስ ራስ ለሆነባት ቤተ ክርስቲያን ስልጣን ራሱን ለማስገዛት የሚፈቅድ ትውልድ ለማፍራት፤
  • በመከባበርና በመቀባበል ላይ የተመሠረት እውነተኛ የወንድማማች መዋደድን ለማሥረጽ፤
  • ለእግዚአብሔር ቃል እውቀት የተሻለ መረዳት ኖሯቸው ተመራቂዎች ቃሉን በበለጠ እንዲጠሙት ለማድረግ፤

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቱ ሰርቲፊኬት ፕሮግራም የሚከተሉትን አራት ዋና ዋና ስነመለኮታዊ ትምህርት ዘርፎች ይዳስሳል።

  • መጽሐፍ ቅዱሳዊ (Biblical) – መቅ ጠቅላላ 10 ክሬዲት ወይም 120 ሰአት
  • ስነመለኮት ጥናት (Theological) – ስመጥ ጠቅላላ 7 ክሬዲት ወይም 84 ሰአት
  • የቤተክርስቲያን ታሪክ (Historical) – ቤክታ ጠቅላላ 3 ክሬዲት ወይም 36 ሰአት
  • አገልግሎት (Ministerial) – አገ ጠቅላላ 12 ክሬዲት ወይም 144 ሰአት