አዲስ ልደት ኢንተርናሽናልቸርች

ድረ-ገጻችንን በመጎብኘት የሚፈልጉትን መረጃ አግኝተው ከእኛ ጋር አብረው ጌታን ለማምለክ ኅብረታችንን እንደሚጎበኙ ተስፋ እናደርጋለን።

እኛ

በሁለት ቦታ ያለ አንድ ቸርች ነን

Silver Spring Maryland

11961 Tech Rd
Silver Spring, MD 20904

ቀጠታ እና የተቀረጹ ቪድዮዎች

Springfield Virginia

8348 Traford Ln. 3rd Floor
Springfield, VA 22152

ቀጠታ እና የተቀረጹ ቪድዮዎች

ራዕያችን

ራዕያችን የመንግስቱን ወንጌል የምታውጅና እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርትን የምታፈራ ቤተክርስቲያን ማየት ነው።

ተልዕኮአችን

ተልዕኮአችን የመንግስቱን ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመስበክ፤ የጽድቅ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ የክርስቶስ ደቀመዛሙርትን በማፍራትና፤ በበጎ ሥራ እየበዛች የምትሔድ ቤተክርስቲያንን በመገንባት የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋፋት ነው።

አገልግሎቶች

የሚያገኙዋቸው አገልግሎቶች

በቸርቻችን የተለያዩ አገልግሎቶችን ያገኛሉ

Silver Spring MD

 

 

ሳምንታዊ አገልግሎቶች

እሁድ
የማለዳ ጸሎት: 10:00am – 11:00am
አምልኮ: 11:00am – 1:30pm
የወጣቶች አገልግሎት: 6:30pm – 9:00pm

የሳምንቱ አጋማሽ
ረብዕ: 6:30pm – 9:00pm
የሃሙስ ጸሎት: 10:00am – 2:00pm

አርብ
አዳር ጸሎት: 8:30pm – 12:30am

Springfield VA

 
 

ሳምንታዊ አገልግሎቶች

እሁድ
የማለዳ ጸሎት: 9:30am – 10:30am

አምልኮ: 10:30am – 1:00pm

የሳምንቱ አጋማሽ
ማክሰኞ: 7:00pm – 9:00pm

አርብ
አዳር ጸሎት: 7:00pm – 11:00pm

ቅዳሜ
የወጣቶች አገልግሎት: 7:00pm – 9:00pm

ስለ እኛ

ስለ ቸርቻችን

428631577_414768224557484_2305014192611984503_n (1)

ታሪካችን

የኅብረታችን ታናሹ ጅማሬ የሚጀምረው ሴፕቴምበር 2008 በዋሽንግተን ዲሲ ነው። ከምስረታው ጥቂት ወራት ቆይታ በኃላ አድራሻችንን ወደ 1010 ሪፕሊይ መንገድ ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ወደ ነበርንበት አዳራሽ ተዛውረን በዚያ ከአስር ዓመታት በላይ ቆይተናል። በ1010 ሪፕሊይ መንገድ ላይ በነበርንበት ጊዜ ቤተክርስቲያናችን በልዩ ልዩ መልኩ በአባላት ቁጥርም በአገልግሎቶችም ስብጥር ዕድገት ታሳይ ነበር። ሁሉም ባርኮት የነበረን ቢሆንም ቤተክርስቲያኗ ባሳለፈቻቸው ከፍታና ዝቅታም መካከል የእግዚአብሔርን ምህረት እና ምግቦቱንም በማይረሳ መልኩ የተካፈልንበትም ነበር።