ስለ እኛ
ታሪካችን
የኅብረታችን ታናሹ ጅማሬ የሚጀምረው ሴፕቴምበር 2008 በዋሽንግተን ዲሲ ነው። ከምስረታው ጥቂት ወራት ቆይታ በኃላ አድራሻችንን ወደ 1010 ሪፕሊይ መንገድ ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ወደ ነበርንበት አዳራሽ ተዛውረን በዚያ ከአስር ዓመታት በላይ ቆይተናል። በ1010 ሪፕሊይ መንገድ ላይ በነበርንበት ጊዜ ቤተክርስቲያናችን በልዩ ልዩ መልኩ በአባላት ቁጥርም በአገልግሎቶችም ስብጥር ዕድገት ታሳይ ነበር። ሁሉም ባርኮት የነበረን ቢሆንም ቤተክርስቲያኗ ባሳለፈቻቸው ከፍታና ዝቅታም መካከል የእግዚአብሔርን ምህረት እና ምግቦቱንም በማይረሳ መልኩ የተካፈልንበትም ነበር።
በ2014 ዓ.ም በአርሊንግተን ቨርጂንያ በሳምንቱ አጋማሽ የተጀመረው የጸሎት እና አምልኮ ምሽት ሁለተኛው የኅብረታችን ታናሽ ጅማሬ የዛሬውን ሁለተኛውን የቤተክርስቲያናችን መገኛ በስፕሪንግፊልድ ቨርጂንያ እንዲኖረን እግዚአብሔር ዕድል ሰጥቶናል። በታናሽ ጉባኤ የተጀመረው የስፕሪንግፊልድ ቨርጂንያ አጥቢያ በዋናነት ትኩረት ሰጥቶ ያገለግል የነበረው በሁለት የቤት ኅብረቶች ውስጥ የነበሩ እና በአሌክሳንድሪያ ቨርጂንያ የነበሩ የቤተክርስቲያናችንን አባላት ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለቱ የቤት ኅብረቶች አድገው ሰባት የቤት ኅብረቶች በቨርጂንያ ውስጥ ብቻ ይገኛሉ። በአሁኑ ጊዜ ሜሪላንድ የሚገኙ የቤት ኅብረቶቻችን ቁጥር 15 ሲሆኑ ቁጥራቸውም ከአመት ወደ አመት በማደግ ላይ ይገኛል።
የአዲስ ልደት ቤተክርስቲያን ቋሚ የማምለኪያ ስፍራ የማግኘት ጥረቷ ጁን 2021 በተከናወነው የህንጻ ግዢ በ 11961 ቴክ ሮድ መንገድ ላይ ያለን ህንጻ የራሷ በማድረግ ያሳካች ሲሆን በተመሳሳይም ሁለተኛውን ህንጻ ደግሞ ለስፕሪንግፊልድ ቨርጂንያ ለመግዛት የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች።
የቤተክርስቲያናችን አመራር
የቤተክርስቲያናችንን አመራሮች ይተዋወቋቸው
የቤተክርስቲያናችን አመራር የተመሠረተው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ የእረኞች የቡድን አመራር መርህን በመከተል ሆኖ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ጠቅላላ ጉባኤ የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪ አካል ነው።

ኤሊያስ ጌታነህ
Pastor - Springfield, VA,ALIC Pastoral Office Associate

ቢኒያም አቦዬ
Pastor - Silver Spring, MD,ALIC Pastoral Office Associate

እሴቶች
አምልኮ
ጸሎት
የወንጌል ስብከት
ደቀመዝሙር ማፍራት
መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ
ክርስቲያናዊ ቤተሰብ
ተተኪ ትውልድን ማፍራት
ክርስቲያናዊ ኅብረት
ሁለንተናዊ አገልግሎት
ራዕያችን
ራዕያችን የመንግስቱን ወንጌል የምታውጅና እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርትን የምታፈራ ቤተክርስቲያን ማየት ነው።
ተልዕኮአችን
ተልዕኮአችን የመንግስቱን ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመስበክ፤ የጽድቅ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ የክርስቶስ ደቀመዛሙርትን በማፍራትና፤ በበጎ ሥራ እየበዛች የምትሔድ ቤተክርስቲያንን በመገንባት የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋፋት ነው።
አስተምህሮ
የእምነታችን መግለጫ፥
በአካልና በስራ ሶስት በመለኮታዊ ባህሪና አምላክነቱ አንድ አምላክ መሆኑን እናምናለን።
በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ብቻ የሚገኝ እንደሆነ እናምናለን።
በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሠረት አማኝ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውሃ እንደሚጠመቅ እናምናለን።
የጌታችን የመድኃኒታችን ስቃይና ሞት የምናስብበትና ሞቱንም የምንናገርበት ቅዱስ ሥርዐት መሆኑንና ስለዚህም ጌታ እስኪመጣ ድረስ በቤተ ክርስቲያን መከናወን ያለበት መሆኑን እናምናለን።
በእግዚአብሔር ቃል መሰረት የተለየና ከሃጢያት የፀዳ ሕይወትን በመለማመድ መንፈሳዊ ፍሬ ማፍራትና ምሳሌነት ያለው ህይወት በመኖር ኢየሱስ ክርስቶስን ከፍ ማድረግ እንደሆነ እናምናለን።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር እንደገና እንደሚመጣ፣ በእርሱ አምነው የሞቱት ቀድመው እንደሚነሱ ሕያዋን የሆኑት ደግሞ እርሱን ለመቀበል እንደሚነጠቁ እናምናለን።
ጻድቃን ከጌታ ጋር ለዘላለም እንደሚኖሩ ኃጢአተኞች ግን ከእግዚአብሔር ፊት ተለይተው በገሃነም እሳት ለዘላለም ተፈርዶባቸው እንደሚሰቃዩ እናምናለን።
የክርስቶስ አካል እንደሆነች በዚህ ምድር ታላቁን ተልዕኮ ለመፈጸም እና የእግዚአብሔርን መንግስት እንድትወክል ስልጣንና ኃላፊነት የተሰጣት እርሷ እንደሆነች እናምናለን።
ያለ ስህተት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እና የመዳን ዕውቀት፣ ለጽድቅ ኑሮ መምሪያን በመስጠት፣ ለሚነሱ የትኛውም ክርክሮችና አስተምህሮዎች የመጨረሻው ወሳኝ ይህ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን።
በክርስቲያናዊ የቤተሰብ እሴቶች እና እንደ እግዚአብሔር ቃል በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል ብቻ በሚደረግ ጋብቻ እናምናለን።
